ጎንደር

From Wikipedia

ከተማው ከላይ ሲታይ የፋሲለደስ ግምብ መያል ላይ
ከተማው ከላይ ሲታይ የፋሲለደስ ግምብ መያል ላይ

ጎንደር የበፊቱ በጌምድር ክፍለ ሐገርና የጥንትዋ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበር። ዛሬ በስሜን ጎንደር ዞነ በአማራ ክልል ሲገኝ፥ ከጣና ሃይቅ ሰሜን አንገረብ ወንዝ ላይ ከሰሜን ተራራ ወደ ደቡብ ምእራብ ሰፍሮ ይገኛል። በሎንጂቱድና ላቲቱደ 12°36′N 37°28′E ላይ ነው።

የማእከላዊ እስታቲስቲክ ባለስልጣን በ1998 ቁጥሩ ጎንደር 194,773 የህዝብ ብዛት ስትይዝ ከነሱም 97,625 ወንዶች ሲሆኑ 97,148 ሴቶች ናችው።